በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሊቢያ ዋና ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ ጎርፍ አስከተለ


የሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ
የሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ

በሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ ትናንት እሁድ ጧት የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የተፈጠረው ጎርፍ ዋና ዋና መንገደኞችን ያጥለቀለቀ ሲሆን ትምህር ቤቶችን ማቋረጡ ተነግሯል፡፡

የትሪፖሊ ደኅንነት ኃላፊ ጥንቃቄ እንዲደረግ የመከሩ ሲሆን፣ በጎርፉ ሳቢያ ተሰናክለው የቆሙ ተሽከርካሪዎችን ከመንገድ የማስወገድ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንአስታውቋል፡፡

በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የተነገረ ዘገባ ባይኖርም የአገሪቱ አየር ትንበያ ማዕከል ሰሜናዊ ሊቢያ ከባድና ነጎድጓዳማ ዝናብ እንደሚኖር መተንበዩ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG