ድሬዳዋ —
በድሬዳዋ የድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ሰራተኞች አስተዳደሩ ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ ሆነን እንድንሰራ እያደረገን ነው ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ። በትናንትናው ዕለት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ያለፉ አንድ የድሬዳዋ ነዋሪ ቫይረሱ እንዳለባቸው ሳይታወቅ ለ10 ቀናት በድልጮራ ሆስፒታል ቆይተዋል።
ለሰውዬው በሆስፒታሉ የህክምና ክትትል ሲያደርጉላቸው የነበሩ የሆስፒታሉ ሰራተኞች ተመርምረው በአስቸኳይ የምርመራ ውጤታቸውን እንዲያውቁ እስከዚያው ድረስም ወደለይቶ ማቆያ እንዲገቡ አለመደረጉ ለሌሎች ህሙማንና ሰራተኞችም ተጋላጭነታችንን የሚጨምር ነው ብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።