በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራና አፋር ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት ድጋፍ ተደረገ


የፌዴራልና የአዲስ አበባ ሆስፒታሎች ድጋፍ
የፌዴራልና የአዲስ አበባ ሆስፒታሎች ድጋፍ

የአዲስ አበባ አስተዳደር፣ የሀረሪ ክልልና የፌዴራል የጤና ተቋማት በአማራና አፋር ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት የሕክምና ቁሳቁሶችና መድሃኒቶች ድጋፍ አበረከቱ። ጉዳት ከደረሰባቸው የሕክምና ተቋምት ውስጥ አንዱን በኃላፊነት እየወሰዱ እንዲያቋቋሙ እንደሚደረግም ታውቋል።

ከዚህ ቀደም የፌዴራሉ ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የሃይቅ ሆስፒታልን መልሶ ለማቋቋም ኃላፊነቱን መውሰዱን አስቀድሞ ያስታወቀ ሲሆን፤ ሌሎች የፌዴራልና የአዲስ አበባ ሆስፒታሎችም እያንዳንዳቸው ከአማራና አፋር ክልል የሚደግፏቸውን የሕክምና ተቋማት ለይተው መረከባቸው ታውቋል።

የሀረሪ ክልልም በዛሬው ዕለት ለሦስት የአፋር ክልል ጤና ጣቢያዎች ድጋፍ የሚውል የሕክምና ቁሳቁሶችንና መድሃኒቶችን ይዞ ወደ አፋር ክልል ማምራቱን አስታውቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።

በአማራና አፋር ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት ድጋፍ ተደረገ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:09 0:00


XS
SM
MD
LG