አዲስ አበባ —
ከመቶ ሃምሳ ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የአሜሪካ መንግሥት ያስገነባው ብሔራዊ የኅብረተሠብ ጤና ማሰልጠኛ ማዕከል ዛሬ በይፋ ተመርቆ ለኢትዮጵያ የኅብረተሠብ ጤና ተቋም ተላለፈ፡፡
ማዕከሉ በብሔራዊ ደረጃ የጤና ክብካቤ ባለሞያዎችን ለማፍራት የሚደረገውን ጥረት በማሳደግና በማስፋት አገልግሎቱን ይበልጥ ፍሬያማ እንደሚያደርገው ይጠበቃል፡፡
በአዲሱ ብሔራዊ የኅብረተሠብ ጤና ማሰልጠኛ ማዕከል ምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ የተሠራጨው የአሜሪካ ኢምባሲ የፁሑፍ መገለጫ እንደሚያብራራው ማዕከሉ የተገነባው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የበሽታዎች ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል ከአሜርካ ፕሬዚዳንት የአስቸኳይ ዕቅድ ለኤድስ ድጋፍ ፔፕፋር ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ነው፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ