የወባ ወረርሽኝ ሥርጭት መጨመር በደቡብ ክልል
ከዐስር ዓመታት በኋላ እንደገና በተቀሰቀሰው የወባ ወረርሽኝ ባለፉት ስድስት ወራት 24 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ። የወረርሽኙ የሥርጭት መጠንም 23 በመቶ መጨመሩን የክልሉ ጤና ቢሮ የበሽታ መከላከል እና ጤና ማጎልበት ዳይሬክቶሬት ዲሬክቴር አቶ ማሌ ማቴ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። በሽታው እንደ አዲስ መሰራጨት የጀመረው የኬሚካል ርጭት ባለመካሄዱ፣ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ይለገስ የነበረው የአልጋ አጎበር በመቋረጡና በመዘናጋር ምክኒያት ተገልጿል። ስርጭቱን ለመግታትም የተጓደሉ ነገሮችን ማሟላት እንደሚያስፈልግ ኃላፊዎቹ ተናግረዋል።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ማርች 14, 2025
በአፍሪካ የኅይል አቅርቦት ላይ ያተኮረውና በዋሽንግተን ዲሲ የተካሔደው ጉባኤ
-
ማርች 14, 2025
የኢትዮጵያውያት ሴቶች ጥያቄ ምንድን ነው? - የአድማጭ ተመልካቾች አስተያየት
-
ማርች 13, 2025
አርቲስት አንዱዓለም ጎሣ ተጨማሪ 13 ቀናትን በእስር እንዲቆይ ፍርድ ቤት ፈቀደ
-
ማርች 13, 2025
ሩሲያ የተቆጣጠረቻቸውን የዩክሬን ግዛቶች እንደያዘች መቀጠል ትሻለች