በሲዳማ ክልል የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር፣ ያለቅድመ ማስጠንቀቂያ የንግድ መደብሮቻችንን እያፈረሰብን ነው፤ ያሉ ነጋዴዎች ቅሬታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገለጡ።
የከተማው የንግድ ማኅበረሰብ አባላት እንደገለጹት፣ የከተማዪቱ አስተዳደር፣ ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ንብረታቸውን የሚያነሡበት የጊዜ ገደብ ሳይሰጣቸው፣ የንግድ ሥፍራቸውን በግብረ ኃይል እያፈረሰባቸው ነው።
የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ በበኩላቸው፣ "የተወሰደው እርምጃ ሕግ የማስከበር ተግባር ነው፤" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።