በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጉራጌ ውስጥ አዲስ ዞን ተጠየቀ


ጉራጌ ውስጥ አዲስ ዞን ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:19 0:00

ጉራጌ ውስጥ አዲስ ዞን ተጠየቀ

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ምሥራቃዊ ክፍል ተወላጆች “ምሥራቅ ጉራጌ ዞን” የሚባል አዲስ አስተዳደር እንዲዋቀር ጠየቁ።

ተወላጆቹ ጥያቄውን ያቀረቡት ዛሬ፤ ሃሙስ ሐዋሳ ከተማ ውስጥ ባካሔዱት ሰላማዊ ሰልፍ ነው።

በተለያዩ እርከኖች ያሉ የአደረጃጀት ጥያቄዎች በአዲሶቹ ክልሎች ምላሽ እንደሚሰጣቸው የክልሉ መንግሥት ገልጿል።

ጥያቄ አቅራቢዎቹ ግን ጥያቄያቸው ምላሽ ያገኛል የሚል እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል።

በየጊዜው በሚነሱ የመዋቅር ጥያቄዎች ላይ የአሜሪካ ድምፅ ሃሳባቸውን ያጋሩ አንድ ምሁር ለችግሩ ምላሽ የሚሰጥበት መንገድ፣ “ሳይንሳዊና በጥናት ላይ የተመሠረተ አለመሆኑን ያሳያል” ብለዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን ዘገባ ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG