በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮሬ ወረዳ ነዋሪዎች አቤቱታ


የኮሬ ወረዳ ነዋሪዎች አቤቱታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:15 0:00

ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ለተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ከደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ኮሬ ብሄረሰብ የተወከሉ ነዋሪዎች "ሸኔ" ብለው በጠሯቸው ታጣቂዎች ይደርስብናል ያሉትን ጥቃት ሸሽተው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥ 28 ሺሕ መድረሱን ተናገሩ።

ፓርላማው በአሸባሪነት የፈረጀውና መንግሥት ሸኔ ብሎ የሚጠራቸው፣ እራሳቸውን ደግሞ “የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት” ብለው የሚጠሩት ታጣቂዎች ይፈፅሙታል በተባለው ጥቃት ምክኒያት፤ ወረዳውን ከሌሎች አከባቢዎች ጋር የሚያገናኘው መንገድ ለተከታታይ ዓመታት መዘጋቱንና ከ200 በላይ ሲቪሎች መገደላቸውን አስታወቀዋል።

በሌላ በኩል አቤቱታቸው እና ተቃውሟቸውን ለማሰማት በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ በር ላይ የተገኙት ተወካዮቹ "በሕዝቡ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት የክልሉ መንግሥት ማስቆም አልቻለም" ሲሉም የክልሉን መንግሥት ከሰዋል።

/አድማጮች የዚህን ዘገባ ዝርዝር ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ/

XS
SM
MD
LG