በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሃሪኬን ሣንዲ


Superstorm Sandy 30 oct
Superstorm Sandy 30 oct

ሃሪኬን ሣንዲ ሕይወት ማጥፋቷ ተዘግቧል፡፡


please wait

No media source currently available

0:00 0:09:30 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


ማዕበሉ ክፉኛ በመታው የምሥራቅ ዩናይትድ ስቴትስ የአትላንቲክ ውቅያኖስ አዋሣኝ ስፋት ያለው ቀጣና ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል፡፡
በዚህም ከስድስት ሚሊየን በላይ ሰው ለችግርና ለጉዳት መጋለጡ እየተነገረ ነው፡፡
በኒው ጀርሲ፣ በኒው ዮርክ፣ በኖርዝ ካሮላይና፣ በከኔክቲከት እና ዌስት ቨርጂንያ ግዛቶች ውስጥ ማዕበሉ እስካሁን የገደለው ሰው ቁጥር ከሠላሣ ማለፉን በቅርቡ የወጡ ዘገባዎች ጠቁመዋል፡፡ /ቪኦኤ ይህንን ዘገባ በዛሬ የአማርኛ ሥርጭቱ ለአየር ባዋለበት ሰዓት የተቆጠረው የ16 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱ ነበር/
ከባዱ ንፋስ ኒው ጀርሲ የባሕር ዳርቻ ሴደርስ ዝነኛዋን የቁማር ጨዋታዎችና የመዝናኛ ሥፍራ አትላንቲክ ሲቲን የመታው እጅግ ከባድ ዝናብ ያስከተለው ኃይለኛና ግዙፍ ጎርፍ ተወዳጅና ታዋቂ የሆነውን ረዥም የባሕር ዳርቻ መንሸራሸሪያ ጎዳና አፈራርሶና አጥቦ ወደ ባሕሩ ወስዶታል፡፡
ሳንዲ ከመድረሷ በፊት አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ ተላልፎላቸው የነበረውን ትዕዛዝና ምክር ሳይሰሙ እዚያው በቀሩ የአትላንቲክ ሲቲ ነዋሪዎች አለመታዘዝ ማዘናቸውን የኒው ጀርሲ አገረገዥ ክሪስ ክሪስቲ ተናግረው ጥሪና ጉትጎታም ያሰሙ ነበር፡፡
ማዕበሉ በኒው ዮርክ ማዕከል በሚገኘው የታችኛው ማንሃታን በታሪክ ተመዝግቦ የማያውቅ እስከ 4.2 ሜትር ከፍታ የደረሰ ጎርፍ አስከትሎ እንደነበርም ታውቋል፡፡
Superstorm Sandy 30 oct
Superstorm Sandy 30 oct

በምሥራቅ ዩናይትድ ስቴትስ ዘጠኝ ግዛቶችና በርዕሰ ከተማይቱ ዋሽንግተን ዲሲ ማክሰኞም የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታው ፀንቶ የዋለ ሲሆን የፌደራል መንግሥቱ መሥሪያ ቤቶች ለሁለተኛ ቀን ዝግ ሆነው ውለዋል፤ የሕዝብ ማመላለሻ አገልግሎቶች ሁሉ እንደተቋረጡ ነው፡፡
የኒው ዮርክ የዓለም ገበያዎች ማክሰኞም ለሁለተኛ ቀን ዝግ ሆነው የዋሉ ሲሆን፣ የገንዘብ ገበያዎቹ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲዘጉ በ114 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡
በረራዎች በመቋረጣቸው በመላ ምሥራቅ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ የአይሮፕላን ጣቢያዎች ላይ ከአሥር ሺሆች የሚቆጠሩ መንገደኞች መንቀሣቀስ አልቻሉም፡፡ የትራንዚት አገልግሎቱም ዝግ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ላለፉት ሦስት ዓመታት በ2 ቢልዮን ዶላር ወጭ እድሣት እየተደረገለት ያለው ባለ 38 ፎቁ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሕንፃ ማዕበሉ አድርሶበታል በተባለ ጉዳት ከተሠራው ብዙው ሳይበላሽ እንዳልቀረ እየተነገረ ነው፡፡
የምድር ቤቶቹ ሁሉ በውኃ መጥለቅለቃቸውንና ለሙሉው ሕንፃ ንፁህ አየር የሚገፋው መሣሪያ በመበላሸቱ ምናልባት ሠራተኞች ረቡዕ ጠዋት ወደ ሥራ ገበታቸው የመመለሣቸውን ነገር አጠራጣሪ ያደረገው መሆኑን አንድ የድርጅቱ ባለሥልጣን ለቪኦኤ አስታውቀዋል፡፡
የዋስትና ሰጭ ኩባንያዎች እንደገመቱት የአሁኑ ጉዳት ክፍያ እስከ ሃያ ቢሊየን ዶላር ሊደርስ ይችላል፡፡
ንፋስና ዝናቡ ዛሬም በአካባቢው እንደቀጠለ ሲሆን ነገ ገለጥ ሣይል እንደማይቀር ሚቲኦሮሎጂስቶች ተናግረዋል፡፡
አካባቢው ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የኢትዮጵያዊያንና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን ማኅበረሰብ የሚኖርበት ሲሆን እስከአሁን በማንም ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የተሰማ ነገር የለም፡፡
ለተጨማሪ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG