አዲስ አበባ —
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የመሪዎች ጉባዔ
የኢትዮጵያው ንጉሥ አፄ ኃይለሥላሴ ለአፍሪካ ያበረከቱትን አስተዋፅዖ የፈተሸ ውይይት ባለፈው ቅዳሜ፤ ኀምሌ 20/2005 ዓ.ም. አዲስ አበባ ላይ ተካሂዷል፡፡
አፄ ኃይለሥላሴ
በአፍሪቃ የኢኮኖሚ ኮሚሽን ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የአፍሪቃ አዳራሽ የተካሄደው የቀድሞው ንጉሥና መንግሥታቸውን ለአፍሪቃ አርነት ትግልና ለአህጉሪቱ ድርጅት ምሥረታ ያደረጉትን አስተዋፅዖ አንስቶ የዘከረውንና የመከረውን መድረክ ያዘጋጀው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ማኅበር ነው፡፡
የአፍሪካ ኅብረት መሥራች አባቶች - ሥዕል፤ አፈወርቅ ተክሌ
በስብሰባው ላይ በክብር እንግድነት ንግግር ያሰሙት የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ፕሬዚደንት ታቦ ምቤኪ አፍሪካ በተለያዩ ተቀናቃኝ ቡድኖች ሳትከፋፈል ለመቆየቷ የንጉሠ ነገሥቱን ሚና አወድሰዋል።
የመለስካቸው አምኃ ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፤ ያድምጡት።