በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቲቢ እየተሸነፈም፤ እያስፈራራም ነው


የዓለም አቅጣጫ የቲቢን መዛመት ማቆም መሆኑን አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥራ ኃላፊ አስታወቁ፡፡

ዶ/ር ኃይለየሱስ ጌታሁን /የዓለም ጤና ድርጅት - ቲቢን እናቁም መርኃግብር/
ዶ/ር ኃይለየሱስ ጌታሁን /የዓለም ጤና ድርጅት - ቲቢን እናቁም መርኃግብር/

ቲቢ እየተሸነፈም፤ እያስፈራራም ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:28 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የዓለም አቅጣጫ የቲቢን መዛመት ማቆም መሆኑን አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥራ ኃላፊ አስታወቁ፡፡

በዓለም የጤና ድርጅት የዓለምአቀፍ የቲቢ፣ የኤችአይቪና የማኅበረሰብ ተሣትፎ መርኃግብር አስተባበሪ የሆኑት ዶ/ር ኃይለየሱስ ጌታሁን ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ ዓለም በቲቢ ላይ አበረታች ውጤት እያስመዘገበ መሆኑንና ሥጋቱም የዚያኑ ያህል ከፍተኛ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ቲቢን እናግኝ፤ እናክመው - የዓለም ቲቢ መቆጣጠሪያ መርኅ
ቲቢን እናግኝ፤ እናክመው - የዓለም ቲቢ መቆጣጠሪያ መርኅ

በአሁኑ ጊዜ የዓለምን ልማቷንና ዕድገቷን ኤድስን ከመሣሰሉት ችግሮች እኩል እያደናቀፈ ያለውንና በፀጥታ ደኅንነቷ ላይም ሥጋት የደቀነው ቲቢ የተረሣ ችግር መሆኑን ለአሜሪካ እንደራሴዎችና ሌሎችም ባለሥልጣናት ለማስረዳት፤ እንዲሁም የፖለቲካና የገንዘብም ድጋፍ ለማግኘት ዋሺንግተን ዲሲ እንደሚገኙ የገለፁት ዶ/ር ኃይለየሱስ በድኅረ ሚሌኒየሙ የልማት ግቦች መርኃግብር መሠረት በመጭዎቹ ሃያ ዓመታት ውስጥ ቲቢን ጨርሶ ለማቆም መታቀዱን አመልክተዋል፡፡

ዓለም ላለፉት ሃያ ዓመታት ከቲቢ ጋር የያዘው ትግል አበረታች ውጤት እያሳየ መሆኑንም ዶ/ር ኃይለየሱስ ገልፀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG