እኒህ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ሰው በለስላሣ ንግግራቸውና በትህትናቸው የሚታወቁ ናቸው ይላል የቪኦኤዋ ማርቴ ፋን ደር ቮልፍ ከአዲስ አበባ የላከችው ዘገባ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በተባለው መሠረት ቃለ-መሃላ ከፈፀሙ በኋላ እስከ 2007ቱ ምርጫ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ሥራ ይረከባሉ፡፡ በሕገመንግሥቱ ላይ የሠፈረው ተፈፃሚ ይሆናል ብለዋል ባለሥልጣናቱ፡፡
አንድ የሥራ ባልደረባቸው ስለአቶ ደሣለኝ ሲናገሩ ትሁት መሆናቸውን አጉልተው የገለፁ ሲሆን ኮስታራም መሆን እንደሚችሉ አመልክተዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ኃይለማርያም ወደ መንበረ ሥልጣኑ የሚዘልቁ ከሆነ ከምጣጥና ቆፍጠን ያለ ወገናቸውንም ለውጭው ዓለም ማሣየት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ደግሞ ቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሣደር ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም “የፖለቲካ ሥልጣን ቅንጣቱ እንኳ በእጃቸው አይገባም” ሲሉ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ የመሰላቸውን አመልክተዋል፡፡
ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡