በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሶማሊያ ስላለው ጦራቸውና ስለምጣኔ ኃብቱ ማብራሪያ ሰጡ


ሶማሊያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር እስካሁን በዚያ መቆየቱ ተገቢ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ገለፁ፡፡




please wait

No media source currently available

0:00 0:05:28 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


ሶማሊያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር እስካሁን በዚያ መቆየቱ ተገቢ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የአፍሪካ ኅብረት ቃሉን አላከበረም” ሲሉ ወቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ሠራዊት ሶማሊያ ውስጥ ባለበት ጊዜ ወጭውን እየሸፈነ ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት እራሱ መሆኑን ያመለከቱት አቶ ኃይለማርያም ጦሩ ወደ ሀገሩ የሚመለስበት ሁኔታ መፋጠን እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ለፓርላማው ባቀረቡት የመንግሥታቸው የስምንት ወር ሪፖርት ላይ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ የመጀመሪያ ሁለት ዓመታት የሃገሪቱ ምጣኔ ኃብት የ10.5 ከመቶ ዕድገት ማስመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከእስክንድር ፍሬው ዘገባ ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG