ወ/ሮ ጽዮን በለጠ “የጽዮና ፉድ” መስራችና ባለቤት ናቸው፡፡ እዚሁ የናይትድ ስቴትስ ውስጥ፣ በሜሪላንድ ሮክቪል የሚገኘው
“የንግሥተ ሳባ ኢትዮጵያ ሬስቶራንት" ባለቤት የነበሩት ወ/ሮ ጽዮን በለጠ፣ እንደ እንጀራና ወጥ የመሳሰሉ ባህላዊ ምግቦችን ቀለል ባሉ ዘመናዊ አቀራረቦችና እሽጎች አሰናድተው ወደ ትልቁ የአሜሪካ ገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡
ባህላዊ ምግቦችን እስከነጣዕማቸው በማዘመን በአሜሪካውያን ደንበኞቻቸው ዘንድ ተወዳጅ እንዲሆን እያደረጉ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ የዜና ማሰራጫዎችም ይህንኑ በመግለጽ አድንቀው ጽፈውላቸዋል፡፡
እንደ እንጀራ ክሪስፕና ከምስር የተሰናዱ በርካታ ምርቶቻቸው እንደ ሆል ፉድ፣ ማምስ ኦርጋኒክ እና ዳውሰንስ ማርኬት በተሰኙ ትላልቅ የአሜሪካ የገበያ መደብሮች ውስጥ በተለያዩ ክፍለ ግዛቶች ውስጥ ተሰራጭተዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያይዘው ፋይል ያድምጡ፡፡