በምሥራቅ ጉራጌ ዞንና በማረቆ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢ፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ አራት የማረቆ ብሔረሰብ አባላት በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን፣ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። “ሟቾቹ ገበያ ውለው በተሽከርካሪ ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ የነበሩ መንገደኞች ናቸው”፤ ያሉት ነዋሪዎቹ፣ በተኩሱ የቆሰሉ ሌሎች ስድስት ሰዎችም በተለያዩ የሕክምና ተቋማት እየታከሙ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። የማረቆ ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ንግሤ መኬ፣ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት ተፈፀመ በተባለው ጥቃት እስከ አሁን የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ስድስት መድረሱን፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ሴፕቴምበር 28, 2024
79ኛው የመንግሥታቱ ጉባዔ አራተኛ ቀን ውሎ
-
ሴፕቴምበር 27, 2024
የመስቀል በዓል በዋሽንግተን ዲሲ
-
ሴፕቴምበር 27, 2024
የ79ኛው የመንግሥታቱ ድርጅት ጉባኤ ሦስተኛ ቀን ውሎ
-
ሴፕቴምበር 26, 2024
የመስቀል ደመራ በዓል ዛሬ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ተከብሯል
-
ሴፕቴምበር 26, 2024
79ኛው የመንግሥታቱ ድርጅት ጉባኤ ሁለተኛ ቀን ውሎ
-
ሴፕቴምበር 25, 2024
ወጣቶችና ቴክኖሎጅ