በምሥራቅ ጉራጌ ዞንና በማረቆ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢ፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ አራት የማረቆ ብሔረሰብ አባላት በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን፣ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። “ሟቾቹ ገበያ ውለው በተሽከርካሪ ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ የነበሩ መንገደኞች ናቸው”፤ ያሉት ነዋሪዎቹ፣ በተኩሱ የቆሰሉ ሌሎች ስድስት ሰዎችም በተለያዩ የሕክምና ተቋማት እየታከሙ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። የማረቆ ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ንግሤ መኬ፣ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት ተፈፀመ በተባለው ጥቃት እስከ አሁን የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ስድስት መድረሱን፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ማርች 14, 2025
በአፍሪካ የኅይል አቅርቦት ላይ ያተኮረውና በዋሽንግተን ዲሲ የተካሔደው ጉባኤ
-
ማርች 14, 2025
የኢትዮጵያውያት ሴቶች ጥያቄ ምንድን ነው? - የአድማጭ ተመልካቾች አስተያየት
-
ማርች 13, 2025
አርቲስት አንዱዓለም ጎሣ ተጨማሪ 13 ቀናትን በእስር እንዲቆይ ፍርድ ቤት ፈቀደ
-
ማርች 13, 2025
ሩሲያ የተቆጣጠረቻቸውን የዩክሬን ግዛቶች እንደያዘች መቀጠል ትሻለች