በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንድ ጠብመንጃ አንጋች አምስት የጋዜጣ ዜና ማደራጃ ሠራተኞቹን ገደለ


አንድ ጠብመንጃ አንጋች አምስቱን የጋዜጣ ዜና ማደራጃ ሠራተኞቹን በገደለ ማግስት አዲስ ይዞት የወጣው ዘገባ የትላንቱን ሰቅጣጭ ድርጊት የተመለከተ ነው።

አንድ ጠብመንጃ አንጋች አምስቱን የጋዜጣ ዜና ማደራጃ ሠራተኞቹን በገደለ ማግስት አዲስ ይዞት የወጣው ዘገባ የትላንቱን ሰቅጣጭ ድርጊት የተመለከተ ነው።

በዩናይትድ ስቴትስ አናፖሊስ ሜሪላንድ የሚገኘው የካፒታል ጋዜጣ ዛሬ በፊት ገጹ ይዞት የወጣው ርዕስ “5 የካፒታል ሠራተኞች በጥይት ተገደሉ” ይላል።

የጋዜጣው የሕዝብ አስተያየት መስጪያ ገጽ ግን ሌጣ ነው። ባጭሩ የሰፈረበት ቃል “ዛሬ ምንም መናገር እንችልም ነገ ጠብቁን” ይላል።

የአናፖሊስ ከተማ ፖሊስ የገዳዩን ማንነት ይፋ ያደረገ ሲሆን ድርጊቱን በፈፀመበት ወቅት የእጅ ቦምቦችና ጠብመንጃ ይዞ ነበር ብሏል።

የፍርድ ቤት ሰነዶች እንደሚያሳዩት ጃሮድ ራሞስ የአምስት ሰዎችን ሕይወት በማጥፋት ተከሷል።

ከጋዜጣ ማደራጃው ድርጅት ጋር ለረዥም ጊዜ የቆየ አለመግባባት እንደነበረው የፖሊስ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG