በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጉጂ ዞን ስምንት ወረዳዎች የፀጥታ ሁኔታ እያሳሰበ ነው

ፎቶ ፋይል፦ በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ መንግሥት ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራቸውና ራሳቸውን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብለው በሚጠሩት ታጣቂ ቡድን “እየደረሰብን ነው” ያሉት ጥቃት ተባብሶ መቀጠሉን የወረዳው ነዋሪዎች ገለፁ።
ፎቶ ፋይል፦ በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ መንግሥት ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራቸውና ራሳቸውን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብለው በሚጠሩት ታጣቂ ቡድን “እየደረሰብን ነው” ያሉት ጥቃት ተባብሶ መቀጠሉን የወረዳው ነዋሪዎች ገለፁ።

በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ መንግሥት ኦነግ ሸኔ ብሎ በሚጠራቸውና ራሳቸውን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብለው በሚጠሩት ታጣቂ ቡድን “እየደረሰብን ነው” ያሉት ጥቃት ተባብሶ መቀጠሉን የወረዳው ነዋሪዎች ገለፁ።

ለደኅንነታቸው እንደሚያሰጋቸው ገልፀው ስማቸው እንዳይገለፅ የጠየቁ ነዋሪዎች፤ የአርሶ አደሮችና የከተማው ነዋሪዎች ከከብቶቻቸው ጀምሮ የተለያዩ ንብረቶች እየተዘረፉባቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

በታጣቂዎቹ ላይ የሚቀርበውን ክስ በተመለከተ ከታጣቂዎቹ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

የወረዳው አስተዳደር በበኩሉ ቡድኑ እያደረሰ ባለው ጥቃት የሰው ሕይወት ማለፉንና ዜጎች መፈናቀላቸውን ገልጦ የክልልና የፌዴራል መንግሥታት ተጨማሪ ኃይል አሰማርተው በዘመቻ እርምጃ ካልወሰደባቸው ሁኔታው አስቸጋሪ መሆኑን አስታውቋል።

ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በጉጂ ዞን ስምንት ወረዳዎች የፀጥታ ሁኔታ እያሳሰበ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:11 0:00

XS
SM
MD
LG