በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ውጊያ እንደተባባሰ የገለጹ የጉጂ ዞኖች ነዋሪዎች “የልጆቻችን ትምህርት አሳስቦናል” አሉ


ውጊያ እንደተባባሰ የገለጹ የጉጂ ዞኖች ነዋሪዎች “የልጆቻችን ትምህርት አሳስቦናል” አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:20 0:00

ውጊያ እንደተባባሰ የገለጹ የጉጂ ዞኖች ነዋሪዎች “የልጆቻችን ትምህርት አሳስቦናል” አሉ

በኦሮሚያ ክልል የጉጂ ዞኖች ልዩ ልዩ ወረዳዎች ነዋሪዎች፣ በመንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል በቀጠለው ግጭት ለከፍተኛ የሰላም ዕጦት እንደተጋለጡ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

ለዓመታት በዘለቀው የጸጥታ ችግር አጋጥሞናል ያሏቸውን ችግሮች ሲያስረዱም፣ ትምህርት ቤቶች ተቋርጠዋል፤ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፤ ማኅበራዊ አገልግሎቶችንም በአግባቡ ለማግኘት አልቻልንም፤ ብለዋል።

ተማሪዎች ልጆቻቸው ለዓመታት ከትምህርት መራቃቸው እንዳሳሰባቸው የገለጹ ነዋሪዎች ላቀረቡት አቤቱታ፥ ከጉጅ፣ ከምዕራብ ጉጂ እና ከምሥራቅ ቦረና ዞኖች የትምህርት ጽ/ቤቶች፣ ከክልሉ የትምህርት ቢሮ እና ከትምህርት ሚኒስቴር፣ አስተያየት እና ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለዛሬ አልተሳካም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG