በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተቃውሞ ሰልፍ በግሪክ


ተቃውሞ ሰልፍ በግሪክ
ተቃውሞ ሰልፍ በግሪክ

በግሪክ የሕዝብ መጓጓዣ ሰራተኞች፣ ተማሪዎችና አስተማሪዎች ባለፈው ሳምንት የተከሰተውንና ለ57 ሰዎች ሕይወት መጥፋት ምክንያት የሆነውን የባቡር አደጋ በመቃወም በማዕከላዊ አቴንስ ሰልፍ አድርገዋል፡፡

መንግሥት ትኩረትና በጀት በመንፈጉና በቂ ሠራተኞች ባለመቅጠሩ የባቡር አገልግሎቱ እጅግ እንዲዳከም ሆኗል በሚል የሥራ ማቆም አድማ ተመቷል፡፡ የግሪክ ዕዳዋ መቆለልም እንደ ምክንያት ይጠቀሳል ሲል ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል፡፡

ባለፈው እሁድ በአቴንስ ከ10ሺህ በላይ ተቃዋሚዎች ሰልፍ ሲወጡ፣ ዛሬም ሌሎች በአሥር ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በአቴንስ እና ሌሎች ከተሞች ሰልፍ አድርገዋል፡፡

በመጪው ሐምሌ የሥልጣን ዘመኑ የሚያበቃው ወግ አጥባቂው የግሪክ መንግሥት የባቡር መጓጓዣውን ችግር እንደሚፈታ ቃል ገብቷል፡፡

XS
SM
MD
LG