በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኅዳሴው ግድብ ዙሪያ ስምምነት ተደረገ


ፎቶ ፋይል፡- የኅዳሴው ግድብ
ፎቶ ፋይል፡- የኅዳሴው ግድብ

በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ግብፅ ዋና ከተማ ካይሮ ውስጥ በተደረገ የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ ድርድር በግድቡ ውኃ አሞላል ሂደት ላይ ከሦስቱም ሀገሮች በሚቀርቡ ሃሳቦች ላይ በተከታይ ዙር ለመነጋገር ተስማምተው ተለያይተዋል።

ኢትዮጵያ በአባይ ላይ የኃይል ማመንጫዎች መሪ ዕቅዷን ተከትላ ግንባታዋን እንደምትቀጥል የውኃ፣ የመስኖና የኃይል ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ አስታውቀዋል።

በካይሮው ውይይት አካሄድና ይዘት ላይ በፅሕፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ዶ/ር ስለሺ ግብፅ ከተለመደው አሠራርና አካሄድ ውጭ የሆነና የሱዳንን የፖለቲካ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያላስገባ ሃሣብ ይዛ ቀርባ እንደነበረ ተናግረዋል።

ይኸው በሦስቱ ሃገሮች መካከል በአባይና በኅዳሴ ግድብ ላይ የሚካሄደው ንግግር ባለፈው ሣምንት እንደገና የተጀመረው ለአንድ ዓመት ያህል ተቋርጦ የከቆየ በኋላ ነው።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኅዳሴው ግድብ ዙሪያ ስምምነት ተደረገ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:29 0:00የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG