አዲስ አበባ —
16ኛው ታላቁ ሩጫ
42 ሺሕ ሰዎች የተሳተፉበት ይሕ ውድድር በሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኋላ የተካሄደ የመጀመሪያው ትልቅ የአደባባይ ዝግጅት ሆኗል፡፡
"የተለያየ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ልዩነታቸውን አቻችለው በአንድነት ሮጠዋል" ሲል የውድድሩ መስራችና ዳይሬክተር ኃይሌ ገ/ሥላሴ ገለፀ፡፡
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ16 ዓመታት፣ ለ16 ጊዜ የተካሄደ የአደባባይ ትዕይንት ሆኖ ቀጥሏል፡፡ በተለይ የዘንድሮው በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ ምክንያት ላይካሄድ እንደሚችል የብዙዎች ጥርጣሬ ነበር፡፡ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም እንዲህ ዓይነት ዝግጅት ሰለመፍቀዱ እርግጠኛ ያልሆኑ ስጋት የገባቸው አልጠፉም፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
-
እስክንድር ፍሬው