በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኅዳሴ ግድብን አስመልክቶ በሚካሄደው ድርድር ኢትዮጵያ አትገኝም


ኢትዮጵያ የኅዳሴ ግድብን አስመልክቶ ነገ ዋሽንግተን ዲሲ በሚካሄደው በዩናይትድ ስቴትስ በሚመራው ቀጣይ ድርድር እንደማትገኝ አስታወቀች። በድርድሩ የማትገኘው ለጊዜው ሊሆን እንደሚችልም አመላክታለች።

የኢትዮጵያ የውሃ መስኖ ኃብት ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው አጭር መግለጫ ነው ይህን ያስታወቀው።

ኢትዮጵያ ተደራዳሪዎችዋን ወደድርድሩ እንደማትልክ ለዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር በኦፊሴል ማስታወቅዋን መግለጫው ጠቁሟል።

“ሀገሪቱ ውስጥ ካሉት ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ የሚደረገው ውይይት ባለመጠናቀቁ በቀጣዩ የድርድር ዙር ልንሳተፍ አንችልም” ይላል መግለጫው።

ኢትዮጵያ ነገ ዋሺንግተን ውስጥ ሊጀመር የታቀደው የኅዳሴ ግድብ ድርድር ላይ አንዳማትሳትፍ ይገለፀችዉ ዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ ሀገሪቱን ጎብኝተው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ጋር ከተነጋገሩ ከሁለት ሳምንታት ባነሰ ጊዜ መሆኑ ነው።

ኢትዮጵያ ግብፅና ሱዳን በኅዳሴ ግድብ ውሃ አጠቃቀም ላይ በዩናይትድ ስቴትስ እና የዓለም ባንክ ታዛቢነት ላልፉት ወራት ሲደራደሩ እንደነበር ይታወሳል።

አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ታላቁ የኅዳሴ ግድብን አስመልክቶ በሚካሄደው ድርድር የዩናይትድ ስቴትስ ሚና እንደሚያሳስብቸው ሲገልፁ ቆይተዋል። ኢትዮጵያ የግብፅን ጥቅም በሚጠብቅ መልክ እንድትስማማ ዩናይትድ ስቴትስ ጫና እየደረገች ነው የሚል ዕምነት እንዳላቸው ይናገራሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG