በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአዲስ አበባ የወርቅ ነጋዴዎች ንብረታቸው በመወሰዱ ችግር ላይ መውደቃቸውን ገለፁ


የአዲስ አበባ የወርቅ ነጋዴዎች ንብረታቸው በመወሰዱ ችግር ላይ መውደቃቸውን ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:16 0:00

በአዲስ አበባ ፒያሳና መርካቶ አካባቢዎች በወርቅ ንግድ የተሰማሩ 30 ነጋዴዎች ከሦስት ወራት በፊት 600 ሚሊዮን ብር የሚገመት ወርቅ በፖሊስ ተወስዶባቸው ሱቃቸው በመዘጋቱ ለችግር መዳረጋቸውን ቪኦኤ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገለፁ።

ነጋዴዎቹ ከ20 ቀናት በላይ ታስረው መቆየታቸውንና በመጨረሻም በዋስ መፈታታቸውን ገልፀው፣ እስካሁን ድረስ ክስ እንዳልተመሰረተባቸው አመልክተዋል፡፡

ጥፋታቸው ምን እንደሆነ በግልፅ የሚነግራቸው አካል ማጣታቸውን የተናገሩት አሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነጋዴዎቹ የደረሰባቸው ችግር ምን እንደሆነ መንግሥት ተረድቶ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

በዚህ ጉዳይ ዙርያ ከአሜሪካ ድምፅ የተጠየቀው የፌደራል ፖሊስ “ጉዳዩ በሕግ የተያዘ በመሆኑ አስተያየት ልሰጥ አልችልም” ብሏል።

የማዕድን ሚኒስቴር ደግሞ “ይህ ጉዳይ እኔን አይመለከትም” የሚል ምላሽ ሰጥቷል፡፡

XS
SM
MD
LG