በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

'ዓለምን በቀጣይ ከሚያሰጓት ወረሽኞች ለመከላከል የሚያጠናው ግሎባል ዋን ሄልዝ ኢንሺየቲቭ' ቆይታ ከፕሮፌሰር ወንድወሰን አበበ ጋር


Wondwossen Abebe Gebreyes PHD
Wondwossen Abebe Gebreyes PHD

ግሎባል ዋን ሄልዝ ኢንሺየቲቭ ወይም አንድ የዓለም ጤና ተነሳሽነት በአሜሪካ ሃገር በሚገኘው በኦሃዮ ስቴት ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት የተመሰረተ ሲሆን ዓላማውም ከአካባቢ፣ ከእንሣት እና ከሰዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው እንደ ኮቪድ 19፣ ኢቦላ፣ የእብድ ውሻ በሽታ፣ በነፍሳት ፣ በውሃ፣ በዓየር..የሚመጡ በሽታዎችን በኢትዮጵያ፣ ኬኒያ፣ ዩጋንዳ፣ታንዛኒያ፣ ሜክሲኮ፣ ብራዚል እና ታይላንድ...እየተንቀሳቀሰ የሚያጠና ነው፡፡ ይሄ ተነሳሽነት ከተመሰረተ ዘንድሮ 10ኛ ዓመቱ ይዟል፡፡

የተላላፊ በሽታዎች እና የሞሎኪውል ጥናት ተመራማሪ እና እና የግሎባል ዋን ሄልዝ መስራች እንዲሁም ዋና ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ወንድወሰን አበበ ገብረየስን በእንግድነት ጋብዘናቸዋል፡፡ ፕሮፌሰር ወንድወሰን ገብረየስ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከመከሰቱ ከ2 ወር በፊት አዲስ አበባ ላይ አድርገነው በነበር ውይይት ላይ በኮቪድም ባይሆን ዓለምን በቅርቡ ወረርሽኝ እንደሚያሰጋት በባለሞያዎች ተወያይተን አውቀነው ነበር ይላሉ፡፡ ተቋማቸው ግሎባል ዋን ሄልዝ ኢንሺየቲቭም እንደኢትዮጵያ ያሉ ታዳጊ ሃገራቶች ላይ የምርምር ጣቢያዎችን በመክፈት፣ በማሰልጠን እና ሌሎች የተለለያዩ የማብቃት ስራዎችን ይሰራል፡፡

ፕሮፌሰር ወንድወሰን አበበ በግሎባል ዋን ሄልዝ ኢንሺየቲቭ ስራዎች ዙሪያ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ዘለግ ያለ ቆይታ አድርገዋል፡፡


XS
SM
MD
LG