በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ማለት ‘ዓለም ማለት ነው’ - ራበርት ሆርማትዝ

ራበርት ሃርማትዝ - የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ራበርት ሃርማትዝ - የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

“የሃሣብና የተግባር መገናኛ ሥፍራ” በሚል መርህ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ እየተካሄደ ያለው ሦስተኛው የዓለም ዳያስፐራ መድረክ የሁለተኛ ቀን ስብሰባውን ቀጥሏል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:09:36 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

“የሃሣብና የተግባር መገናኛ ሥፍራ” በሚል መርህ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ እየተካሄደ ያለው ሦስተኛው የዓለም ዳያስፐራ መድረክ የሁለተኛ ቀን ስብሰባውን ቀጥሏል፡፡
የዓለም ዳያስፐራ መድረክ - 2013 በዋሽንግተን ዲሲ
የዓለም ዳያስፐራ መድረክ - 2013 በዋሽንግተን ዲሲ
ስብሰባው በዛሬው ውሎው ከተለያዩ ሃገሮች ወደአሜሪካ ገብተው በረዥም ጉዟቸው ስኬታማና ታዋቂ የሆኑ ሰዎችን ታሪኮች ከራሣቸው አንደበት አዳምጧል፡፡
የቪኦኤ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ኤንሶር ዓለምአቀፏን ሱፐር ሞዴል ሊያ ከበደን በዓለም ዳያስፐራ ፎረም - 2013 ላይ ሲያነጋግሩ
የቪኦኤ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ኤንሶር ዓለምአቀፏን ሱፐር ሞዴል ሊያ ከበደን በዓለም ዳያስፐራ ፎረም - 2013 ላይ ሲያነጋግሩ
ዓለምአቀፏ ሱፐር ሞዴል - ኢትዮጵያዊቷ ሊያ ከበደ፣ በማራቶን የኦሊምፒክ ሜዳሊስቱ፣ የኒው ዮርክ ማራቶን አሸናፊውና በጎ አድራጊው ኤርትራዊው መብ ክፍለዝጊ፣ ከአንዲት የቱርክ መንደር ተነስተው “በአሜሪካ ቁጥር አንድ” የተባለ የእርጎ አምራች ኩባንያ ባለቤት የሆኑ ሥራ ፈጣሪና መዋዕለ-ነዋይ አፍሣሽ ይገኙበታል፡፡

በስብሰባው መግቢያ ላይ የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራበርት ሃርማትዝ የዳያስፐራው ማኅበረሰብ ለዩናይትድ ስቴትስ “ቋንቋዎችን፣ ባሕሎችን፣ የሥራ ዕድሎችን፣ በንግድ ሥራ ውስጥ አደጋዎችንና ሥጋቶችን የመጋፈጥ፣ የማሸነፍና የማስወገድ ልምድን፣ የሣይንስና የቴክኖሎጂ ሃሣቦችንና ችሎታን፣ እንዲሁም የበጎ ፍቃደኝነት መንፈስን ይዞ የመጣ ነው” ብለዋል፡፡

የቪኦኤ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ኤንሶር ዓለምአቀፏን ሱፐር ሞዴል ሊያ ከበደን በዓለም ዳያስፐራ ፎረም - 2013 ላይ ሲያነጋግሩ
የቪኦኤ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ኤንሶር ዓለምአቀፏን ሱፐር ሞዴል ሊያ ከበደን በዓለም ዳያስፐራ ፎረም - 2013 ላይ ሲያነጋግሩ
በዛሬው መድረክ ላይ ቀርባ የነበረችው ዓለምአቀፍ ሱፐር ሞዴል ሊያ ከበደ የዓለም የጤና ድርጅትም ዓለምአቀፍ አምባሣደር ነች፡፡ ሊያን በመድረኩ ላይ ያወያይዋት የአሜሪካ ድምፁ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ኤንሶር ናቸው፡፡

የሦስተኛው የዓለም ዳያስፐራ መድረክ ስፖንሰር ከሆኑ ኩባንያዎችና የሚድያ ተቋማት መካከል የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ አንዱ ነው፡፡

ለዝርዝርና ለተጨማሪ መረጃ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG