በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ዳያስፐራ መድረክ በዋሽንግተን ዲሲ


የዓለም ዳያስፐራ ፎረም - 2013
የዓለም ዳያስፐራ ፎረም - 2013




please wait

No media source currently available

0:00 0:04:54 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የዓለም ዳያስፐራ መድረክ - 2013 በዋሽንግተን ዲሲ
የዓለም ዳያስፐራ መድረክ - 2013 በዋሽንግተን ዲሲ
በዓለም ዙሪያ ከሃገሮቻቸው ውጭ የሚኖሩ ሰዎች እምቅ አቅም ለየወጡባቸው ሃገሮችና ማኅበረሰቦች ጥቅም ሊውል የሚችልባቸውን ሁኔታዎች ለማበረታታት የታሰበው የዓለም ዳያስፐራ መድረክ ዋሽንግተን ዲሲ ላይ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

በመድረኩ ላይ በበርካታ የግል የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ የሚሠሩ ስመ ገናና ኢትዮጵያዊንና ኤርትራዊያን እየተሣተፉ ሲሆን ከዓለም ዙሪያ የዳያስፐራው አባላት የሆኑ ከአንድ መቶ በላይ ሃገሮች የተገኙበት ነው፡፡

የዛሬ ሦስት ዓመት ተጠንስሶ ለሦስተኛ ጊዜ እየተካሄደ ያለው ዓለምአቀፍ የዳያስፐራ መድረክ “የሃሣብና የተግባር መገናኛ ሥፍራ” የሚል መርኅ ያለው ነው፡፡

የትውልድ ሃገሩን እየጣለ ወደ ሌሎች ሃገሮች የሚፈልሰው ሰው ቁጥር ባለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ በሦስት እጥፍ የጨመረ ሲሆን ዛሬ በዓለም ዙሪያ ከ215 ሚሊየን በላይ ሰው በውጭ እንደሚኖር በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡

ሰዎች ሃገሮቻቸውን እየጣሉ የሚወጡት በኢኮኖሚ ምክንያቶች፣ ደህንነት ፍለጋና በውጭ ከሚኖሩ ቤተሰቦቻቸው ጋር ለመቀላቀል ሲሆን ከሚወጣው ሰው የበዛወ ግን ከትውልድ ሃገሩ ጋር ያለው ቁርኝት እንደቀጠለ እንደሚኖር በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡

ዶ/ር ራጅ ሻህ - የዩናይትድ ስቴትስ የዓለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲ - ዩኤስኤአይዲ ዋና አስተዳዳሪ

የዓለም ባንክ ባወጣው መረጃ መሠረት በዓለም ዙሪያ በዳያስፐራ ከሚኖሩ ሰዎች ወደ ትውልዳቸው ወይም ወደ ሌሎች ሃገሮች የተንቀሣቀሰው ገንዘብ በ2011 ዓ.ም 381 ቢሊየን ዶላር መድረሱን እና ይህ ቁጥር በመጭዎቹ ዓመታት ከሰባት እስከ ስምንት ከመቶ በሆነ መጠን እያደገ እንደሚሄድ የዩናይትድ ስቴትስ የዓለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲ - ዩኤስኤአይዲ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ራጅ ሻህ ገልፀዋል፡፡

የሦስተኛው የዓለም ዳያስፐራ መድረክ ስፖንሰር ከሆኑ ኩባንያዎችና የሚድያ ተቋማት መካከል የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጣቢያ አንዱ ነው፡፡

ለዝርዝርና ለተጨማሪ መረጃ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG