በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአዲስ አበባዉ የመንግስታቱ ድርጅት የዓለም አቀፍ የልማት ጉባኤ ተጠናቀቀ


please wait

No media source currently available

0:00 0:04:22 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


ላለፉት አራት ቀናት አዲስ አበባ በሚገኙ የመንግስታቱ ድርጅት የስብሰባ ማእከልና ሆቴሎች ሲከናወን የነበረዉ ሶስተኛዉ ”ፋይናንስ ለልማት ዓለም አቀፍ ጉባኤ” ዛሬ 134 አንቀጾች ያሉት ”የአዲስ አበባ የተግባር አንጀንዳ” በማስደቅ ተጠናቋል።

ሰነዱ ላለፉት ስምንት ወራት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አማካይነት ዝርዝር ሥራዎች ሲከናወኑበት እንደነበር ተገልጿል።

የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ በጉባኤዉ ማጠቃለያ ላይ በዓለም አቀፍ ግንኙነት ጎልተዉ የሚታዮ ችግሮችን በመጋፈጥ የሰዉ ልጆችን እጣ ፈንታ የተሻለ አቅጣጫ እንዲይዝ በማስቻል የዓለም መሪዎችን አመስግነዋል።

በጉባኤዉ ማጠቃለያ ላይ ንግግር ያደረጉ የUnited States ተወካይ በበኩላቸዉ የመልማት መብት ዓለም አቀፋዊ መግባባት እንደሌለዉ በመጥቀስ አገራቸዉ ግን ከሰብአዊ መብቶች መከበር ጋር መያያዝ እንዳለበት ታምናለች ብለዋል።

ዝርዝሩን ከመለስካቸዉ አመሃ ሪፓርት ያድምጡ

XS
SM
MD
LG