በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመን አቶ አንዳርጋቸውን አሳልፋ ትሰጥ ይሆን? ባለሙያው ‘እንደሕጉ አትችልም’ ይላሉ


አቶ አንዳርጋው ፅጌ
አቶ አንዳርጋው ፅጌ

please wait

No media source currently available

0:00 0:09:03 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

please wait

No media source currently available

0:00 0:15:40 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በኢትዮጵያ መንግሥት በሽብር ድርጅትነት የተፈረጀው የግንቦት ሰባት የፍትሕ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በጉዞ ትራንዚት ላይ ሳሉ የመን ዋና ከተማ ሰንዓ ውስጥ ባለፈው ሣምንት ሰኞ፣ ሰኔ 16/2006 ዓ.ም ተይዘው እስካሁን በየመን መንግሥት እጅ እንደሚገኙ ግንቦት ሰባት ባወጣውና ሊቀመንበሩ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ለቪኦኤ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

አቶ አንዳርጋቸው ለምን እንደተያዙ እስከአሁን የሚታወቅ ምክንያት የለም፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የየመን መንግሥት አቶ አንዳርጋቸውን በሌሉበት ከስሦ የሞት ቅጣት ላስፈረደባቸው ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፎ ሊሰጣቸው ይችላል የሚል ሥጋት ያደረበት መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሕግ ማብራሪያ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው አሜሪካ የነዋሪ የሆኑት የሕግ ጠበቃ አቶ ፍፁም አቻምየለህ ሲናገሩ “በ1984 ዓ.ም /እአአ/ ተግባራዊ በሆነውና የመንም ፈራሚ ሃገር በሆነችበት ዓለምአቀፍ ስምምነት መሠረት አቶ አንዳርጋቸውን እንድትሰጥ ሕጉ አይፈቅድላትም” ብለዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዙትን የዘገባና የቃለ-መጠይቅ ሙሉ ቃል ፋይሎች ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG