በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋና ፕሬዚዳንት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ራሳቸውን አገለሉ


የጋና ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ አዶ
የጋና ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ አዶ

የጋና ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ አዶ ኮሮናቫይረስ ከያዘው ሰው ጋር በቅርበት መገናኘታቸውን ተከትሎ ለሁለት ሳምንታት ራሳቸውን ለይተው እንደሚገኙ ተገለፀ።

የፕሬዚዳንቱ የቅርብ ሰው የሆኑ ቫይረሱ በምርመራ ስለተገኘባቸው ፕሬዚዳንቱ ራሳቸውን አግልለው እንዲቀመጡ ሃኪማቸው በሰጧቸው ምክር መሰረት መሆኑን ነው ቃል አቀባያቸው የገለጹት።

ፕሬዚዳንቱ ምርመራ ተደርጎላቸው ከቫይረሱ ነፃ እንደተባሉ ነገር ግን ለጥንቃቄ ሲሉ ራሳቸውን እንደለዩ ቃል አቀባዩ አክለው ገልፀዋል።

የምዕራብ አፍሪካዊቱ ሃገር እስካሁን በምርመራ የተገኙት የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች ቁጥር አሥራ ዘጠኝ ሺህ የደረሰ ሲሆን 117 ሰዎች ሞተዋል።

XS
SM
MD
LG