በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ቀሪ ኑሯችንን በጋና” ያሉ ጥቁር አሜሪካውያን ተመላሾች ቁጥር እየጨመረ ነው


“ቀሪ ኑሯችንን በጋና” ያሉ ጥቁር አሜሪካውያን ተመላሾች ቁጥር እየጨመረ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:09 0:00

ጋና እ.አ.አ ከ2019 ዓ.ም ወዲህ፣ ጥቁር አሜሪካውያን ኑሮአቸውን በሀገሯ እንዲያደርጉ ስታበረታታ ቆይታለች፡፡ “ወደ ሥረ መሠረታችኹ ተመልሳችኹ ትስስር ፍጠሩ፤ ሀብታችኹን በማፍሰስ እየሠራችሁ ኑሩ!” በማለት ጥሪ በማሰማት ላይ ትገኛለች፡፡

ቻዝ ካይዘር፣ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ኑሯቸውን በጋና ያደረጉ ጥቁር አሜሪካዊት ናቸው፡፡ በተለይ እንስት ጥቁር አሜሪካውያን፣ የእርሳቸውን ፈለግ እንዲከተሉ ያበረታታሉ፡፡ ኑሯቸውን በጋና ለማድረግ የሚያስቡ ሴቶችን እንደሚረዱ ይገልጻሉ፡፡ ዐዲስ መጪዎቹ የወጠኑት የንግድ ሥራ ዕቅድ እውን ይኾንላቸው ዘንድ ድጋፍ ይሰጣሉ፡፡

ቻዝ ካይዘር፣ “ሴሬኒቲ ሀውስ ጋና” በሚል ስም በአቋቋሙት ድርጅታቸው፣ ብቻቸውን ወደ ጋና ተጉዘው የማረፊያ እና የምክር አገልግሎት ለሚሹ ሴቶች ድጋፍ እንደሚሰጣቸውና ሥራም እንደሚያፈላልግላቸው አስታውቀዋል፡፡

ከአክራ በሴናኑ ቶርድ የተጠናቀረውን ዘገባ፣ ከዛሬው አፍሪካ ነክ ርእሶች አንዱ አድርገነዋል፡፡

XS
SM
MD
LG