በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ ጆርጂያ የሴነት ተወካዮች ምርጫና ትውልደ ኢትዮጵያውያን


ዶ/ር ኤባ ከድር ኤባ
ዶ/ር ኤባ ከድር ኤባ

በቅርቡ ከተጠናቀቀው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ጋር የህዝብ ተወካዮችና እንደራሴዎች ምርጫም አብሮ ሲካሄድ መቆየቱን ይታወቃል፡፡ በተለይም ሪፐብሊካን የሚቆጣጠሩትን የሴኔት ምክር ቤት ውጤት በመቀየር አብላጫውን ወንበር ሊያገኙ ይችላሉ የተባሉት የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ሳያሸንፉ ቀርተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ጆርጂያ ግዛት በተካሄደው ምርጫ የሁለቱም ፓርቲ ተፎካካሪዎች ለአሸናፊነት የሚያበቃቸውን ድምጽ ማግኘት ባለመቻላቸው፣ ምርጫው በድጋሚ እንዲካሄድ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

ጆ ባይደን የበለጠ አቅም እንዲኖራቸውና ትልሞቻቸውን ያለ ተቀናቃኝ ማስፈጸም እንዲችሉ ሁለቱንም ምክር ቤቶች በዴሞክራቶቹ አጋሮቻቸው ሥር መዋል ይኖርባቸዋል፡፡ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላትም በሴንቱ ያላቸውን የበላይነት ይዘው ለመቆየት በጆርጅያ ግዛት ሚደረገው ምርጫ ከሆነ ሁለቱንም፣ ካለሆነም ቢያንስ አንደኛውን እንኳ ማሽነፍ ይኖርባቸዋል፡፡ በዚህ የተነሳ፣ የጆርጂያው የሴነት ምርጫ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ፣ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ የዚህ ምርጫ ሂደትና ውጤቱ ይነካል ብለው ያመኑ፣ በጂርጆያ ግዛት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንም፣ በልዩ ትኩረት እየተከታተሉና አንዳንዶቹም እየተሳተፉ መሆኑን እዚያው ጆርጂያ ውስጥ፣ አትላንታ ከተማ የሚኖሩት ዶ/ር ኤባ ከድር ይናገራሉ፡፡ በሙያቸው የህጻናት ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ኤባ ከድር ኤባ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ጆርጅያ ግዛት አትላንታ ከተማ ነዋሪ ናቸው፡፡ ከኤትራውያንና ሶማሌ ዜጎች ጋር በመሆን መራጮች በምርጫው እንዲሳተፉ እያደረጉት ስላለው ጥረት እንዲነገሩን የኢትዮጵያውያን በአሜሪካ እንግዳ አድርገናቸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ፋይል ያድምጡ፡፡

በአሜሪካ ጆርጂያ የሴነት ተወካዮች ምርጫና ትውልደ ኢትዮጵያውያን
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:28 0:00


XS
SM
MD
LG