በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራ የማዕድንና የኤነርጂ ሚኒስትር ጄኔራል ስብሐት ኤፍሬም ጥቃት ደረሰባቸው


የኤርትራ የማዕድንና የኤነርጂ ሚኒስትር ጄኔራል ስብሐት ኤፍሬም
የኤርትራ የማዕድንና የኤነርጂ ሚኒስትር ጄኔራል ስብሐት ኤፍሬም

የኤርትራ የማዕድንና የኤነርጂ ሚኒስትር ጄኔራል ስብሐት ኤፍሬም ከሁለት ቀናት በፊት ወደ ቤታቸው ሲያመሩ በደረሰባቸው ጥቃት በፀና ቆስለው በኦሮታ ሆስፒታል ሲታካሙ ከቆዩ በኋላ ዛሬ ወደ ውጭ ሃገር እንደተላኩ ተገልጿል።

የኤርትራ የማዕድንና የኤነርጂ ሚኒስትር ጄኔራል ስብሐት ኤፍሬም ከሁለት ቀናት በፊት ወደ ቤታቸው ሲያመሩ በደረሰባቸው ጥቃት በፀና ቆስለው በኦሮታ ሆስፒታል ሲታካሙ ከቆዩ በኋላ ዛሬ ወደ ውጭ ሃገር እንደተላኩ ተገልጿል። አንዳንድ ምንጮች በሽጉጥ ተመተው ነው ይላሉ። የሚታመኑ የሚባሉ ምንጮች ደግሞ ተደብድበው ነው እንደሚሉ ተግልጿል።

ጥቃት ያደረሰባቸው ሰው ተይዞ እየተመረመረ መሆኑን ስማቸው እንዲገልጽ ያልፈለጉ ሰዎች ተናግረዋል ተብሏል። ከፖሊስም ሆነ ከባለሥልጣኖች ማረጋገጫ አልተገኘም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG