ከሦስት ዓመታት በኋላ ወደ መቐለ የተጓዙት፣ የዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲ እና ሉዓላዊነት ፓርቲ የሥራ አስፈጻሚ አቶ ገብሩ ዐሥራት፣ በትግራይ ሕዝብ ላይ ከፍተኛ በደል መድረሱን ተናገሩ።
ትግራይን መነሻ አድርጎ በሰሜን ኢትዮጵያ ለኹለት ዓመታት የዘለቀው ጦርነት እንዳይጀመር፣ በፓርቲያቸው በዓረና በኩልም ኾነ በግላቸው ሐሳብ በመስጠት ጥረት አድርገው የነበረ ቢኾንም፣ ሳይሳካላቸው መቅረቱን ገልጸዋል፡፡ ጦርነቱ፣ በሁሉም ወገን ደም አፋሳሽ እና አሳዛኝ እንደነበር ቁጭታቸውን ተናግረዋል፡፡
ጦርነቱ፣ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶርያ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ስምምነት የተደረገበት ዕለት፣ “በጣም የተደሰትኹበት ቀን ነው፤” ያሉት አቶ ገብሩ፣ ችግሩን ለዘለቄታው በፖለቲካዊ መንገድ እልባት ለመስጠት፣ “በክልሉ ይኹን በአገር አቀፍ ደረጃ፣ ሁሉም ሓሳቦች እና ኃይሎች የሚወከሉበት እውነተኛ አካታች ውይይት ያስፈልጋል፤” ሲሉ አመልክተዋል፡፡
መቐለ የሚገኘው ዘጋቢያችን ሙሉጌታ አጽብሓ፣ አቶ ገብሩን አነጋግሯቸዋል፡፡ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።