በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዳግም ግጭት ሰዎች ያለሕግ እየታሰሩ መኾናቸው ተገለጸ

 በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዳግም ግጭት ሰዎች ያለሕግ እየታሰሩ መኾናቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:17 0:00

በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዳግም ግጭት ሰዎች ያለሕግ እየታሰሩ መኾናቸው ተገለጸ

በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ ከልዩ ወረዳ አደረጃጀት ጥያቄ ጋራ በተያያዘ ዳግም ከተቀሰቀሰው የጸጥታ ችግር ጋራ በተያያዘ፣ ቢያንስ ከ60 በላይ ሰዎች ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ መታሰራቸውን፣ የቤተሰብ አባላት እና የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቀዋል፡፡

ከታሳሪዎቹ ውስጥ፣ በግጭቱ ዙሪያ ለቪኦኤ አስተያየት ሰጥተው የነበሩ ቄስ አስሬ ፋቴ እና አራት ቀሳውስት እንደሚገኙበት ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ ከአካባቢው ባለሥልጣናት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG