በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሙርሌ ታጣቂዎችና የጋምቤላ ክልል ሥጋት


የሙርሌ ታጣቂዎችና የጋምቤላ ክልል ሥጋት
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:39 0:00

ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው በመግባት “በተደጋጋሚ ጥቃት ያደርሳሉ” ሲል የክልሉ መንግሥት አስታወቀ። ጥቃቶቹን ለማስቆም በደቡብ ሱዳንና ጋምቤላ ክልል ድንበር አካበቢ ሰላም ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ሥምምነት ላይ መደረሱንም የክልሉ መንግሥት አመልክቷል።

በተያያዘ ርዕስ ታጣቂዎቹ ባለፈው ሳምንት ውስጥ በተመሳሳይ የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው ገብተው በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ውስጥ ባደረሱት ጥቃት አንድ ሰው ገድለው ሌላ አንድ ሰው ማቁሰላቸው ተዘግቧል።

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ የሚፈጽሙት ጥቃት መንስኤ ምንነትና ማስቆም የሚቻልበትን መንገድ አስመልክቶ ጥናቶች መስራታቸውን የገለጹ አንድ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ መምሕር በጉዳዩ ዙሪያ ትንታኔ ሰጥተውናል።

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG