በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋምቤላ ከተማ የታጣቂዎች ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ


 በጋምቤላ ከተማ የታጣቂዎች ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:49 0:00

በጋምቤላ ከተማ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ ታጣቂዎች በአንድ የመዝናኛ ክበብ ውስጥ በከፈቱት ተኩስ፣ ዘጠኝ ሰዎች መቁሰላቸውን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

የጋምቤላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልም፣ የጥቃቱ ሰለባ የኾኑ ሰዎችን ተቀብሎ እያከመ መኾኑንና፣ ከመካከላቸው ከባድ ጉዳት የደረሰበት አንድ ሰው፣ ለተሻለ ሕክምና ወደ አዲስ አበባ እንደተላከ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል፡፡

የክልላዊ መንግሥቱ፣ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ደግሞ፣ በጥቃቱ ዘጠኝ ሰዎች መቁሰላቸውን አረጋግጦ፣ ጥቃት ፈጻሚዎቹ ግን “እስከ አሁን አልተያዙም፤” ብሏል፡፡

ዝርዝር ዘገባዉን ከተያያዘው ፋይል ይመልከቱ፡፡

XS
SM
MD
LG