በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋቦን መፈንቅለ መንግሥት የተሳተፉ ታሰሩ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የጋቦን መንግሥት ቃል አቀባይ ዛሬ ማለዳ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ያደረጉት ወታደሮች ካለ አንድ በስተቀር ሁሉም ታስረዋል ሲሉ አስታውቀዋል።

የጋቦን መንግሥት ቃል አቀባይ ዛሬ ማለዳ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ያደረጉት ወታደሮች ካለ አንድ በስተቀር ሁሉም ታስረዋል ሲሉ አስታውቀዋል።

አራት ታስረዋል አንዱ ግን አምልጧል ብለዋል የጋቦን መንግሥት ቃል አቀባይ ጋይ በርትራንድ።

ወታደራዊ መኮንኖች ዛሬ በመዲናይቱ ሊብረቪል የሚገኘውን የጋቦን ብሄራዊ ሬድዮ ተቆጣጥረው ነበር።

የብሄራዊ መልሶ ማቋቋም ካውንስል የመመስረት ዓላማ እንድላቸው ገልፀው ነበር።

ፕሬዚዳንት አሊ ቦንጎ በቅርቡ በሬድዮ ያደረጉት ንጝር በራቸው ለመቀጠል ባላቸው ብቃት ላይ ጥርጣሬ አሳድሯል ሲሉ ሌተና ኬሊ ኦንዶ ኦብያንግ በራድዮ ተናግረው ነበር።

ፕሬዚዳንቱ በገጠማቸው ስትሮክ ወይም በአንጎል ውስጥ የደም ቧምባ መዘጋት ምክንያት ሞሮኮ እየታከሙ ናቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG