በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የዛፍ ጥላ ስር ውይይት”


“የዛፍ ጥላ ስር ውይይት”
“የዛፍ ጥላ ስር ውይይት”

ፈቲያ መሃመድ ትባላለች፥ ተወልዳ ያደገችው ድሬዳዋ ነው። ሞዴሊስት ነች። በግንቦት 2019 አሜሪካ ላይ በተካሄደ የዓለም የማኅበረሰብ አገልግሎት ወይዘሮ ዓለም አሸናፊ ነች። ይህንን ድሏን ተጠቅማ የአካባቢዋን ማኅበረሰብ ለማገልገል ወጤታማ እንቅስቃሴ አካሂዳለች።

“የዛፍ ጥላ ስር ውይይት”
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:49 0:00

ፈቲያ በዘርፉ የዳበረ ልምድ ካላቸው ሞዴሎች ተርታ ትሰለፋለች፤ በጃፓንና ቻይና በተካሄዱ የወይዘሪት አለም ቁንጅና ውድድሮች ላይ ተሳታፊ የነበረችው ፈቲያ ትዳር መስርታ ልጅ ከወለደች በኋላም በወይዘሮዎች መካከል በሚካሄዱ አለም አቀፍ ውድድሮች ተደጋጋሚ ድሎችን አስመዝግባለች። በግንቦት 2019 አሜሪካ ላይ በተካሄደ የአለም የማህበረሰብ አገልግሎት ወይዘሮ አለም አሸናፊ ነች። ይህንን ድሏን ተጠቅማ የአካባቢዋን ማህበረሰብ ለማገልገል ወጤታማ እንቅስቃሴ አካሂዳለች።

ፈቲያ ብዙ ጊዜዋን ባሳለፈችበት ሞዴሊንግና ፋሽን ላይ ብቻ ከማተኮር ይልቅ በአሜሪካ አሸናፊ የሆነችበትን የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት መርጣ ወደ ድሬዳዋ አቅንታለች። በድሬዳዋ ሙከጀላ የሚባል ቀደምት ባህል አለ። ሙከጀላ ኅብረተሰቡ በመካከሉ ያለውን አለመግባባት ዛፍ ጥላ ስር ሆኖ የሚመክርበት ባህል ነው። በመተሳሰብና በፍቅር ይታወቅ የነበረው የድሬዳዋ ነዋሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተደጋጋሚ በግጭት ስሙ መነሳቱ የከነከናት ፈቲያ ይሄ መስተካከል አለበት በሚል ነባሩ የሙከጀላ ወይም የዛፍ ጥላ ስር ውይይት በዘመናችንም መደገምና ችግሩ መፈታት አለበት ብላ ተነሳች።

ለዚህም አርቲስት አሊቢራ፣ አረቲስት አሊሽቦ፣ ወይዘሮ የትነበርሽ ንጉሴ፣ ከንቲባ መሃመድ አህመድ ቡህ፣ ኡጋዞች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ሌሎችም የድሬዳዋ ጉዳይ ይመለከታቸዋል የተባሉ ልይሎች ተጽእኖ ፈጣሪ 150 ታዋቂ ሰዎች በጋራ የሚመክሩበትን መድረክ ፈጥራለች።

ፈቲያ ያሰበችው ተሳክቶ ወጤታማ የዛፍ ጥላ ስር ውይይት ተካሂዷል። ይህ በግል ተነሳሽነት የተጀመረ እንቅስቃሴ ብዙዎችን ለተመሳሳይ እንቅስቃሴ ያነሳሳ ነበር። ፈቲያ በወጣትነቷ ያገኘችውን እውቅና ተጠቅማ የትውልድ አካባቢዋን ችግር ለመፍታት እንደሞከረችወ ሁሉ ሌሎች ወጣቶችም በየተሰማሩበት ዘርፍ ለማህበረሰባቸው የሚችሉትን እንዲያደርጉ ጥሪ ታቀርባለች።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG