በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቡድን 7 የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህና ተጠያቂነት እንዲኖር ጠየቁ


አዲስ አበባ
አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መካከል የተደረሰውን የሠላም ስምምነትና ያንን ተከትሎም የሚታየውን አዎንታዊ ለውጥ በበጉ እንደሚቀበሉት በጃፓን በስብሰባ ላይ የሚገኙት የቡድን 7 የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

የቡድን 7 ሰባት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ የአፍሪካ ሕብረት በሠላም ስምምነቱ ላይ የተጫወተውን ሚና አድንቀዋል፡፡ በተጨማሪም የሽግግር ፍትህና ተጠያቂነት እንዲሠፍን የሚደረገው ጥረት እንዲጠናከር ጠይቀዋል፡፡

የሠላም ስምምነቱን ሙሉ ለሙሉ በመተግበር ረገድ ሁለቱም ወገኖች ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ፣ እንዲሁም ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ተቆጣጣሪዎች ካለገደብ እንዲቀሳቀሱ እንዲፈቀድ ጠይቀዋል፡፡

በሱዳን በጦር ሠራዊቱና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ያወገዙት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ፣ ካለምንም የቅድሚያ ሁኔታ ግጭቱን እንዲያቆሙ ጥሪ አድርገዋል፡፡

በሶማሊያ ፕሬዚዳንት እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደትና ከአል ሻባብ ጋር የሚደረገው ፍልሚያ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግለት ጠይቀዋል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ ሠላምና ጸጥታን ማስፈን፣ የሰብዓዊ ፍላጎትን ማሟላት እና ከችግሮች መልሶ የማገገምን አቅም ማሳደግ አጣዳፊ ጉዳዮች መሆናቸውን በጃፓን በስብሰባ ላይ ያሉት የቡድን 7 የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባወጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG