በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሊቢያ ጉብኝት

ከምዕራባውያን ሀገሮች የፖለቲካ ሰዎች መካከል ሊብያን በቅርቡ በመጎብኘት የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዣን-ኢቭ ሊድሪያን አንዱ ሲሆኑ፣ ትናንት ሰኞ ከሊብያ የተለያዩ የፖለቲካና ወታደራዊ ተቀናቃኝ መሪዎች ጋር ውይይት አካሄደዋል።

ከምዕራባውያን ሀገሮች የፖለቲካ ሰዎች መካከል ሊብያን በቅርቡ በመጎብኘት የፈረንሳይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዣን-ኢቭ ሊድሪያን አንዱ ሲሆኑ፣ ትናንት ሰኞ ከሊብያ የተለያዩ የፖለቲካና ወታደራዊ ተቀናቃኝ መሪዎች ጋር ውይይት አካሄደዋል።

የፈረንሳዩ ባለሥልጣን ካነጋገሯቸው መካከል አንዱ፣ በምሥራቃዊ ክፍል የነዳጅ አምራች አካባቢ ይዞታቸውን የሚያጠናክሩት የጦር አበጋዙ ካሌፋ ሃፍጣር ሲሆኑ፣ ሌላው ደግሞ ከሊብያው የአንድነት መንግሥት ጋር የሚሰሩት ፋይዝ አል ሰራጄ ናቸው።

እነዚህ ሁለቱ ተቀናቃኝ ወገኖች ወደ አንድነት ለመምጣት፣ በአሁኑ ወቅት ያልተረጋጋ የሥልጣን ክፍፍል መኖሩን የአውሮፓ ዲፕሎማቶች አመልክተዋል።

ፈረንሳይ የሊብያን ቀውስ ለማርገብ ተደጋጋሚ ሙከራና ጥረት ማድረጓ የሚታወቅ ቢሆንም ኢጣልያ ግን፣ የፈረንሳይን ጥረት “በወጉ ያልተቀነባበረ” ስትል ትነቅፋለች።

የፈረንሳዩ መሪ ኢማኑኤል ማርክሮን፣ የጦር አበጋዙን የጀነራል ሃፍታረን አካሄድ ይደግፋሉና፣ ፈረንሳይ ሀቀኛ እርቀ ድርድር ማካሄድ አትችልም በማለት፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG