በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእንግሊዝ የባሪያ ፈነጋዩን ሃልውት የነቀሉ ፍ/ቤት ቀረቡ


እንግሊዝ ውስጥ እኤአ ከ1985 ጀምሮ በ17ኛው ክፍለ ዘመን የነበረውን የባሪያ ፈንጋይ ሃውልት ነቅለው በመጎተት ከወንዝ ጨመረው የጣሉ አራት ሰዎች ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተሰማ፡፡

በምዕራብ ብሪታኒያ ውስጥ ተነቅሎ የተጣለው የነሃስ ሃውልት ብሪስቶል ከተማ ውስጥ የሚገኘው የኤድዋርድ ኮልስተር የተባለው የባሪያ ነጋዴ መሆኑን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ድርጊቱ የተፈጸመው እኤአ ሰኔ 7/2020 ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በነጭ ፖሊስ የተገደለውን ጆርጅ ፍሎይድን ግድያ በመቃወም አደባባይ በወጡ የብላክ ላይቭ ማተርስ ወይም የጥቁሮች ህይወት ዋጋ አለው ተቃዋሚዎች መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ከዚያ ጊዜ ወዲህ ከኮልስተር ስም ጋር የተያያዘ ንግድ ያላቸው ሰዎች ከስያሜው እየራቁና ስም እየለወጡ መምጣታቸው ተነግሯል፡፡

በተነቀለው ሃውልት ምትክ የአንድ ተቃዋሚ ሴት ጊዜያዊ ምስል በቦታው የተተካ ቢሆንም ወዲያውኑ በመንግሥት መወገዱ ተገልጿል፡፡

በወቅቱ መላ እንግሊዝን አጥለቅልቆ በነበረው የጸረ ዘረኝነት ተቃውሞ፣ የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ተወዳጅ ጀግና መሆናቸው የሚነግርላቸውና በምክር ቤቱ ህንጻ አጠገብ የነበረው የሁለተኛው ዓለም ጦርነት መሪ ዊንሰተን ቸርችል ሀውልት፣ “ይሄ ዘረኛ” በሚል ጽሁፍ ተበላሽቶ እንደነበርም በዘገባው ተመልክቷል፡፡

የእንግሊዝ መንግሥት እንዲህ ዓይነቱን ታሪካዊ ቅርሶችን የማያጠለሹና የሚያበላሹ ሰዎች ላይ ጥብቅ እርምርጃ እንዲወሰድ የሚያስችል ህግ እንዲወጣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጆንሰን አስተዳደር ግፊት እያደረገ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ኦክስ ፎርድ ውስጥ ታዋቂ ግለሰቦች የተሳተፉበት ተቃውሞም በ19ኛው ክፍለዘ ዘመን የቅኝ አገዛዝ አራማጁ የሲሲሊ ሮድ ሀውልት እንዲወገድ መጠየቁም በአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG