አዲስ አበባ —
የቀድሞውን የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ መሐመድ ኡመርን ጨምሮ አራት የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በግድያና በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው መያዛቸውን ፖሊስ ለፍርድ ቤት አመለከተ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው በደል እንደተፈፀመባቸውና የዋስ መብታቸው ተከብሮ እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡
ፍ/ቤቱ ለብይን ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።