በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሺሕ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከሱዳን መውጣታቸውን ውጭ ጉዳይ አስታወቀ


please wait

No media source currently available

0:00 0:05:03 0:00

በሱዳን በሁለቱ የጦር ጀነራሎች መካከል የሚካሔደው ውጊያ ተከትሎ፣ እስካሁን ከ3 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያን ከሱዳን መውጣታቸውን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

ከኢትዮጵያውያኑ በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ የ61 ሀገራት ዜጎችም በኢትዮጵያ በኩል መውጣታቸውን እና 75 የበረራ ፈቃዶች መሰጠታቸውንም የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ተናግረዋል፡፡

ከ1400 በላይ ሱዳናውያንም በስደት ወደ ኢትዮጵያ ስለመግባታቸው ገልጸዋል፡፡ በሌላ ዜና፣ የጀርመን መራሄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ የገቡ ሲኾን፣ በግጭት ለተጎዳው የሰሜን ኢትዮጵያ መልሶ ማቋቋም የሚኾን ድጋፍ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

XS
SM
MD
LG