በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በውጭ ምንዛሬ ለውጡ ሳቢያ የግል የቴሌቭዥን ጣቢያዎች እየተዘጉ ናቸው


በውጭ ምንዛሬ ለውጡ ሳቢያ የግል የቴሌቭዥን ጣቢያዎች እየተዘጉ ናቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:56 0:00

የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ምንዛሬ ፖሊሲ ለውጥ ማድረጉን ተከትሎ፣ የሳተላይት ስርጭት ኪራዩ በእጥፍ በመጨመሩ ለመክፈል መቸገራቸውንና ስርጭታቸውን አቋርጠው ለመውረድ መገደዳቸውን፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ የቴሌቭዥን ሓላፊዎች ተናግረዋል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ባገኘው መረጃም መሠረት፣ በሳተላይት ስርጭታቸውን ከሚያስተላልፉ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች መካከል እስከ አሁን 13 የሚኾኑቱ ከሳተላይት ወርደዋል፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ተግባቦት ትምህርት ክፍል መምህር የኾኑት ዶክተር አየለ ዐዲስ በበኩላቸው፣ በአሁኑ ወቅት በብዙኀን መገናኛዎች መካከል ፍትሐዊ ያልኾነ የማስታወቂያ ገቢ ክፍፍልን ጨምሮ ሌሎችም ጫናዎች ምኅዳሩን ለግል የቴሌቭዥን ጣቢያዎች አዳጋች አድርገውታል፤ ይላሉ፡፡ በጣቢያዎቹ ሓላፊዎች ቅሬታ ላይ ምላሽ የጠየቅናቸው፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ሓላፊዎች፣ በጉዳዩ ላይ ማጣራት እያደረጉ ስለመኾኑ በጽሑፍ መልዕክት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG