በአዲስ አበባ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው የደስታ መንደር ከፌስቱላ ህመም ያገገሙ ሴቶች ቀጣይ ህይወታቸውን ለመምራት የሚያስችላቸውን የሥነልቦና እና የሥራ ፈጠራ ሥልጠና ያገኛሉ፡፡
ሥልጠናው ህይወታቸውን ለመቀየር እንደሚያስችላቸው የሚገልጹት ሰልጣኞቹ፣ የራሳቸውን ህይወት ተሞክሮ በማጋራት ፌስቱላን ለመከላከል ለአካባቢያቸው ነዋሪዎች ግንዛቤ እንደሚፈጥሩም ተናግረዋል፡፡
በአረንጓዴ የተሸፈነው የማዕከሉ ገጽታ፣ በቆይታቸው መንፈሳቸውን እንደሚያድስም ሰልጣኞቹ እና የማዕከሉ ነዋሪዎች ይገልጻሉ፡፡