በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ከበጀት አፋፏ ከመውደቅ ተረፈች

ሕጉ በተወካዮች ምክር ቤት የሕግ መምሪያ 257 ለ 167፣ በሕግ መወሰኛው ውስጥ 89 ለ 8 በሆኑ ድምፆች ፀድቋል
ሕጉ በተወካዮች ምክር ቤት የሕግ መምሪያ 257 ለ 167፣ በሕግ መወሰኛው ውስጥ 89 ለ 8 በሆኑ ድምፆች ፀድቋል

የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ አውጭዎች ባለፈው ዓመት ማብቂያ እና ትናንትን የከረሙበት ትንቅንቅ ሌሊቱን በከፊል መፍትሔ አግኝቶ አድሯል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:11:59 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ መሪ ኤሪክ ካንቶር፣ አፈ ጉባዔው ጆን ቤነር እና ሌሎች ሪፐብሊካን እንደራሴዎች
የተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ መሪ ኤሪክ ካንቶር፣ አፈ ጉባዔው ጆን ቤነር እና ሌሎች ሪፐብሊካን እንደራሴዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ አውጭዎች ባለፈው ዓመት ማብቂያ እና ትናንትን የከረሙበት ትንቅንቅ ሌሊቱን በከፊል መፍትሔ አግኝቶ አድሯል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ብዙ ሲሠጋበት በቆየው የበጀቷ አፋፍ በመድረሷ ብዙዎችን ያለማቋረጥ ሲያነጋግር የበረው የምጣኔ ሃብት ድቀት አደጋ በመጠኑም ቢሆን የተወገደ ይመስላል፡፡

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና ምክትላቸው ጆ ባይደን፣ በሕጉ ደስተኞች ናቸው
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና ምክትላቸው ጆ ባይደን፣ በሕጉ ደስተኞች ናቸው

በዚህ በአዲሱ የበጀት ሕግ መሠረት ዩናይትድ ስቴትስ በመጭዎቹ አሥር ዓመታት ውስጥ እጅግ ከበርቴ ከሚባሉ ከፋዮች በሚሰበሰብ ግብር መንግሥቷ የ600 ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ ገቢ ያገኛል፡፡

ሕጉ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ከወታደራዊና ከሃገር ውስጥ ወጭዎች ለመጭዎቹ ሁለት ወራት እንዳይቆረጥ የጊዜ ፋታ ይሠጣል፤
  • የወተትና የወተት ምርቶች ዋጋ እንዳይጨምር የሚደነግጉ ሕግጋት ዘመን ይራዘማል፤
  • አዛውንትን የሚያክሙ ባለሙያዎች የሚገባቸውን ክፍያ እንዳያገኙ የሚከለክለውን ሕግ ያግዳል፤
  • የሥራ አጥነት ክፍያ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ለሁለት ሚሊዮን አሜሪካዊያን እንዲራዘም ያደርጋል፤
  • ለተወካዮች ምክር ቤት አባላት ይከፈል የነበረውን የ900 ዶላር የኑሮ ማካካሻ ተጨማሪ ወርኃዊ ክፍያ ይሠርዛል፤
  • ልጆች ላሏቸው፤ እንዲሁም ለኮሌጅ ክፍያና ለታዳሽ ኢነርጂ የሚሰጡ የታክስ ቅነሣዎችን ያራዝማል፡፡
ፍልሚያው ምን ይመስል ነበር? ለምን? ዛሬስ ሰዎች ምን ይላሉ?
ዘገባውን ያዳምጡ
XS
SM
MD
LG