በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦሚክሮን ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ታየ


ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ
ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ

ኦሚክሮን የተባለው የኮቪድ-19 ዝርያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዩናይትድ ስትቴትስ በምዕራብ ካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ መታየቱ የጤና ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡

ቫይረሱ የታየባቸው ግለሰብ ህዳር 22 ከደቡብ አፍሪካ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የተመለሱ ሲሆን ባላፈው ሰኞ በተደረገላቸው ምርመራ ኦሚክሮን ቫይረስ በውስጣቸው መገኘቱ ተረጋግጧል፡፡

ይህን ያረጋገጡት የዩናይትድ ስቴትስ የተላላፊ በሽታዎች ከፍተኛ ባለሙያና የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የጤና ጉዳዮችና ዋና አማካሪ ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ ሲሆኑ፣ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ግለሰቡ መጠነኛ የኮሮናቫይረሰ የህመም ምልክት የታየባቸው ሲሆን ራሳቸውን አግልለው በመቆየት እየተሻላቸው መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

ግለሰቡ ሁሉቱንም ክትባቶች አሟልተው የወሰዱ ሲሆን የማጠናከሪያውን ክትባት ግን ገና ያልወሰዱ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ፋውቺ በሚቀጥሉ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ቫይረሱን የተላላፊነት መጠንና የትኞቹ የክትባት ዓይነቶች የተሻለ ውጤት ሊያመጡ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ሊደርሱበት ይችሉ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG