በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በ “ፍኖተ-ነፃነት” ጉዳይ የአንድነትና የመንግሥት ምልልስ


“ፍኖተ-ነፃነት”

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፥ «ፍኖተ ነፃነት» ለተሰኘው ሣምንታዊ ጋዜጣው ሕትመት መቋረጥ የኢሕአዴግን መንግሥት ተጠያቂ አድርጓል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:50 0:00
ቀጥተኛ መገናኛአንድነት ዛሬ ረፋዱ ላይ ባወጣው የፅሁፍ መግለጫ እንዳስታወቀው ከአንድ ወር በፊት በብርሃንና ሠላም ማተሚያ ድርጅት “አላትምም” ባይነት የተቋረጠው የፓርቲው ልሣን የ“ፍኖተ-ነፃነት” ጉዳይ አንድምታው ሰፊ ነው፡፡
የጋዜጣዋ ሕትመት የተቋረጠው በአታሚው ድርጅት በብርሃንና ሠላም አስተዳደራዊ ውሣኔ ነው ቢባልም በአንድነት ፓርቲ ተቀባይነት ያገኘ አይመስልም፡፡
ድርጅቱ የመንግሥት በመሆኑ ትዕዛዙ ከመንግሥት እንደመጣም የፓርቲው መሪዎች ይናገራሉ፡፡
ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ለማፈን መንግሥት ይወስዳቸዋል ከሚላቸው እርምጃዎችም አንዱ እንደሆነ መግለጫው ያስረዳል፡፡ እንዲያውም የአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ያወጣው ይህ መግለጫ በርዕሱ ላይ በጉልህ ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በማፈን ለሚከሰተው አደጋ ኃላፊነቱን የሚወስደው ኢሕአዴግ የሚመራው ነው ይላል፡፡
በጉዳዩ ላይ መልስ የሰጡት የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሺመልስ ከማል ለቪኦኤ ሲናገሩ ክሡ “መሠረተ ቢስ ነው” ብለዋል፡፡
አክለውም ብርሃንና ሠላም የማንንም ሥራ ላለመቀበል ሕጋዊ የሆነ መብት እንዳለው ገልፀዋል፡፡
ዝርዝሩን ከመለስካቸው አምሃ ዘገባ ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG