በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል ከመቶ ሺሕ በላይ የትራኮማ ተጠቂዎች ሕክምና እንዳላገኙ ተገለጸ


በአማራ ክልል ከመቶ ሺሕ በላይ የትራኮማ ተጠቂዎች ሕክምና እንዳላገኙ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:50 0:00

· የካርተር ማዕከል የዘመቻ ሕክምና እያካሔደ ነው

በአማራ ክልል ሕክምና ያላገኙ፣ ከ100 ሺሕ በላይ የዐይን ማዝ ወይም የትራኮማ በሽታ ታማሚዎች መኖራቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ፣ ብዙ የበሽታው ታማሚ የሚገኘው፣ በአማራ ክልል ውስጥ እንደኾነ የገለጹት፣ በቢሮው የትራኮማ በሽታ ቴክኒካዊ አማካሪ አቶ ስንታየሁ አወቀ፣ የጤና ቢሮው አማራ ክልል ከሚገኘው የካርተር ማዕከል ከተሰኘው ዓለም አቀፍ ገባሬ ሠናይ ድርጅት ጋራ በመኾን፣ በሽታውን ለማጥፋት እየሠራ ይገኛል፤ ብለዋል፡፡

ካለፉት 15 ዓመታት ወዲህ፣ በክልሉ ትራኮማን ለማጥፋት እየሠራ ያለው የካርተር ማዕከል የተሰኘው ዓለም አቀፍ ገባሬ ሠናይ ድርጅት፣ ከያዝነው ሳምንት አንሥቶ፣ የዘመቻ ሥራ እንደ ጀመረ ገልጾ፣ እስከ አሁን ከ750 ሺሕ በላይ ለሚኾኑ ዜጎች ሕክምና መስጠቱን አስታውቋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG